የምርጥ ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከላት መሰረታዊ መረጃ
- ባህር ዳር ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከል የተቋቋመበት ዓ.ም 2005
- እንጅባራ ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከል የተቋቋመበት ዓ.ም 2005
- ኮምቦልቻ ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከል የተቋቋመበት ዓ.ም 2006
- ደብረብርሃን ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከል የተቋቋመበት ዓ.ም 2008
- ቻግኒ ምርጥ ዘር ብዜት ጣቢያ የተቋቋመበት ዓ.ም 2004
- ብርሸለቆ ምርጥ ዘር ብዜት ጣቢያ የተቋቋመበት ዓ.ም 2010
የኢንተርፕራይዙ ዓላማዎች
- የተለያዩ የሰብልና የእንሰሳት መኖ ዘሮችን ቅድመ መስራች፣ መስራች እና የተመሰከረለት ዘር በራሱ የእርሻ መሬት በግል ድርጅቶችና በአርሶ አደር ማሳ ላይ ጥራቱን የጠበቀ ዘር በማባዛት አዘጋጅቶ ለደንበኞች ማቅረብ፣
- አስፈላጊ የሆኑና ለክልሉ የተለያዩ የአየር ቀጠናዎች ተስማሚ የሆኑ የሰብልና የመኖ አዝርእትን ከውጭ ሀገር በማስገባት ለአርሶ አደሮች ማሰራጨት፣
- በክልሉ ውስጥ የዘር ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣
የኢንተርፕራይዙ ራዕይ
የአማራ ክልል አርሶ አደሮችንና በግብርና ዘርፍ የተሰማራውን ባለሃብት የዘር ፍላጐት በማሟላት ወደ ኢንዱስትሪው ዕድገት ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት እገዛ የሚያደርግ እና በዘር ኢንዱስትሪው በክልልም ሆነ አገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጠንካራ የሆነ የዘር ኢንተርፕራይዝ ተፈጥሮ ማየት
የኢንተርፕራይዙ ተልዕኮ
ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እና የእንስሳት መኖ ዘሮችንና ችግኞችን ከተለያዩ ምርምር ማዕከላትና ከውጭ ሃገር በመግዛትና በማስገባት ሳይንሳዊ የአመራረት ሥርዓትን ተከትሎ በማምረትና በማዘጋጀት ለክልሉ አርሶ አደሮችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ማቅረብ
የኢንተርፕራይዙ እሴቶች
- ጥራት ያለው ምርጥ ዘር ማቅረብ መገለጫችን ነው፣
- ተባብረን በሕብረት በመስራት የአርሶአደሩን የምርጥ ዘር ፍላጐት በማሟላት ኑሮው እንዲሻሻል እናደርጋለን፣
- ታታሪነት፣ ተወዳዳሪነትና ጥራት መለያችን ነው፣
- ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመዘርጋት ለተገልጋዮች ፈጣን አገልግሎት እንሰጣለን፣
- ወጭ ቆጣቢ የሆነ አሠራር በመከተል ኢንተርፕራይዙን ትርፋማ እናደርጋለን፣
- ኢንተርፕራይዙን ተወዳዳሪና ትርፋማ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን፣
- በጠንካራ መሰረት ላይ የሚገነባ ውጤታማ ተቋም እንዲሆን እንጥራለን፣